መንፈሳዊ የዕውቀት ማዕከል

የፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ታሪክና አገልግሎት

የሕፃናት፣ የወጣቶችና የአበው መንፈሳዊ የእውቀትና የአገልግሎት ማዕከል

Students studying

የፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት የምሥረታ ታሪክ

የሆሳዕና መንበረ ጵጵስና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት የምሥረታ ታሪክ ሰንበት ትምህርት ቤት የዖታ የዕድሜ ገደብ ሳይደረግበት ክርስቲያኖች በዘመናቸው በዕለተ እሁድ እየተሰበሰቡ መሠረት የሆነውን የቤተክርስቲያን ሃይማኖት ትምህርቱን፣ ትውፊቱን፣ ታሪኩንና ሥነ-ምግባር እየተማሩ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ጠንካራ ሆነው የሚያድጉበት፤ መልካም ዜጋን የሚያፈሩበት፤ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን የሚማሩበት፤ ለቤተክርስቲያንም ለሃገርም መልካም ትውልድ የሚፈራበት በእንቅስቃሴያቸውም ሆነ በመልካም ሥራቸው አርአያ የሚሆኑ በየአካባቢው በሚሄዱበት ቦታ ወንጌልን ትውልድን የሚያስተምሩ መንፈሳውያንን የምታፈራ ናት። የሆሳዕና መንበረ ጵጵስና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤትም በመልካም ስማቸው ከሚጠቀሱ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ተጠቃሽ ነው።

በብፁህ ወቅዱስ አቡነ ጎርጎርዮስ የወንጌል አገልግሎት የፈሩ በአከባቢው የነበሩ የሳቸው የመንፈስ ልጆቻቸው የመሰረቷት የሆሳዕና መንበረ ጵጵስና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት እንደ ሰንበት ትምህርት ቤት የተመሰረተችው በመስከረም 21 ቀን 1981 ዓ.ም በወጣት ወንድማገኝ ሾላ በአሁን ስማቸው ቆሞስ አባ አብርሃም አማካኝነት ተመሰረተች በወቅቱ ምንም አይነት መሰባሰቢያ ቤት ባይኖራቸውም በቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ እየተገናኙ የምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን፣ ትምህርተ ሃይማኖት ፣የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ እነዚህን ትምህርቶች መምህራንን በመመደብ ያስተምሩ ነበር ። የደብሩ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እየጨመሩ በመምጣቱ ሲሰባሰቡበት የነበረው ደጀ ሰላም እየጠበበ ሲመጣ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ ለመስራት በሀሳብ ተስማሙ ነገር ግን ይህን ሀሳብ ወደ ስራ ለማውረድ አቅም ስላልነበራቸው ሁሉም ጊዜ በፍቅር ሆነው ይጸልዩ እንደነበር በወቅቱ የነበሩት አባላት ይናገራሉ ።

ከብዙ ፈተናዎች በኋላ በእግዚአብሔር እርዳታ በተለያዩ መንገዶች የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ከተሰራ በኋላ በ1985 ከደጀ ሰላም ወደ አዲስ ሰንበት ትምህርት ቤት መግባት ተችሏል። ነገር ግን ከጥቂት አመታት ቆይታ በኋላ አሁን የተሰራው ሰንበት ትምህርት ቤት ከጊዜ ቆይታ ምክንያት እየፈረሰ ሲመጣ አዲስ ስንብት ትምህርት ቤት የመስራት ሀሳብ እንደገና ተነሳ ስንብት ትምህርት ቤቱም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መልከፀዴቅ መልካም ፍቃድ አሁን እንደ ቤተ መቅደስ ሆኖ የሚያገለግለውን ሰንበት ትምህርት ቤት በሐምሌ 11 በ1989ዓ.ም የመሰረተ ድንጋይ ተጣላ የሰንበት ትምህርት ቤቱን ስራም ለማጠናቀቅ እንድ አመት የፈጀ ሲሆን በ1990 ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት ላይ ዋለ። የፈለገ ህይወት ሰንበት ትምህርት ቤት አሁን ላይ ከ500 መቶ ያላነሱ አባላትን በውስጡ በትምህርት እንዲሁም በአገልግሎት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የሰንበት ትምህርት ቤቱ አሁናዊ መሪዎችና አባቶቻችን

በአሁኑ ወቅት ሀገረ ስብከቱን፤ ደብሩን እና ሰንበት ትምህርት ቤቱን በመንፈሳዊ አገልግሎት በኃላፊነት እየመሩ የሚገኙ መሪዎች

ቢንያም
የሰ/ት/ቤት መሪ / ሊቀመንበር

ዲያቆን ቢንያም

የሆሳዕና መንበረ ጵጵስና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ፈለገ ህይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሊቀ መንበር፡፡

ቆሞስ አባ ወልደትንሳኤ ባህሩ
የደብሩ አስተዳዳሪ

መልአከ ኤዶም ቆሞስ አባ ወልደትንሳኤ ባህሩ

የሆሳዕና መንበረ ጵጵስና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ።

ህርያቆስ
የሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ህርያቆስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሀዲያና ስልጤ ሀጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል::

ራእይና ተልዕኮ

የሰንበት ትምህርት ቤታችን ዓላማ

የሰንበት ትምህርት ቤታችን ዋነኛ ዓላማ ሕፃናትና ወጣቶች በኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ ሃይማኖታቸው ጸንተው እንዲያድጉ፣ መጽሐፍ ቅዱስንና የቤተክርስቲያንን ሥርዓት እንዲማሩ ማድረግ ነው።

✓

በሃይማኖትና በምግባር የታነጸ ክርስቲያናዊ ትውልድ ማፍራት

✓

የያሬዳዊ ዜማና የቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት ማስተማር

Students

የሰንበት ትምህርት ቤቱ የትምህርት ክፍላት

በየደረጃው ላሉ አባላት የሚሰጡ የተለያዩ የመንፈሳዊ ትምህርት ዘርፎች

የሕፃናት ክፍል

ከ 5 - 12 ዓመት ለሆኑ ህፃናት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችና ሥነ-ምግባር

የወጣቶች ክፍል

የነገረ-መለኮት፣ የቤተክርስቲያን ታሪክና የክርስቲያናዊ ህይወት ጥናት

የመዝሙር ክፍል

ያሬዳዊ መዝሙራትና የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች ጥናት ክፍል

የግዕዝ ክፍል

የግዕዝ ቋንቋ፣ ሰዋስው እና የዜማ መጻሕፍት ጥናት